Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል- የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ የነበረው የጸጥታ ችግር በግብርና፣ በኢንቨስትመንት እና በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሳው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የነበረውን የጸጥታ እና የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት ሕግ የማስከበር ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ በክልሉ በጸጥታ መዋቅሩ ውስጥ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ 1 ሺህ 900 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

ሌሎች የተለያዩ ወንጀሎች የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማማጣት እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ሕግ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል አቶ ደሳለኝ፡፡

ክልሉ የጀመረው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.