Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እጥረትን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተደጋጋሚ የሚታየውን የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር የአማራ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ውይይት አካሄደ ።

በውይይቱ  የክልል የንግድና ገቢያ ልማት ሀላፊዎች፣ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች የነዳጅ  ማደያ ባለቤቶች፣ የዞን የየንግድና ገቢያ መመሪያ  ሀላፊዎች  ተሳትፈዋል።

የክልሉ የንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ተዋቸው ወርቁ እንደገለፁት በክልሉ የነዳጅ አቅርቦትና የስርጭት   ችግር መኖኑን በፅሁፍ አቅርበዋል ።

ከዚህ ባለፈ የጥቁር ገቢያ ሽያጭ እና የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ በፌድራል  ሊፈቱ የሚችሉ የህግ ማቀፍ፣ የፍትሃዊነት እና ሌሎችም ችግሮች  በምክንያትነት  ተጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ  የነዳጅ ማደያዎች  ቁጥር ማነስ እና የነዳጅ ማስፋፊያ  በክልሉ አለመኖር  ዋናዎቹ ችግሮች  መሆናቸውን  አቶ ተዋቸው አንስተዋል።

ተሳታፊዎች  በበኩላቸው  ለነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት  እጥረት ዋናው ችግር መንግስት የአቅርቦት  ችግሩን  መፍታት  አለመቻሉ ነው ብለዋል ።

ተሳታፊዎች አክለውም  የመንግስት  ህገወጥነትን  በመቆጣጠር  በኩል ደካማ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን  በረጅም እና በአጭር ጊዜ ለመፍታት  ,እየተሰራ  መሆኑን አቶ ተዋቸው ገልፀዋል።

በረጅም  ጊዜ ውስጥም  በክልሉ  በአዲስ 812 ነዳጅ ማደያዎች  ለመግባት  እየተሰራ ሲሆን እስካሁን 119ቱ ቦታ ተሰጥቷቸው  ለመገንባት በዝግጅት  ላይ መሆናቸውን  አስረድተዋል።

100 የነዳጅ ማከፋፈያ ቦታ ከክልሉ መንግስት ተጠይቆ እስካሁን 10 የነዳጅ ማከፋፈያዎች መገንባታቸውንም ገልፀዋል።

ከአጭር ጊዜ አኳያም የጥቁር ገቢያ ሽያጭን ለመቆጣጠር  ከምሽቱ 1 ስአት እስከ ጧቱ 12 ስአት የነዳጅ  ሽያጭ እንዲቆም እና የቀን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የነዳጅ አቅርቦት እና የስርጭት እጥርት ችግር  የሚቆጣጠር  ግብር ሀይልም ከአጋር አካላት ጋር መቋቋሙ ተጠቅሷል።

በናትናኤል ጥጋቡ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.