Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የከተራና የጥምቀት በዓል ያለምንም ችግር መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የከተራና የጥምቀት በዓል ያለምንም ችግር መጠናቀቁን የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ከተራና ጥምቀት በዓል ያለምንም ችግር በደማቅ ሁኔታ ከነሙሉ ኃይማኖታዊ ክዋኔው በሰላም፣በፍቅር፣በደስታ ተከብሮ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
በዓሉ ሌሎች የእምነት ተከታዮች፣ የውጭ አገር ቱሪስቶች፣ አርቲስቶች፣ ታላላቅ የእምነት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ ክልሎችና አጎራባች አገራት የተጋበዙ የሉካን አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ መከበሩንም ተናግረዋል፡፡
አቶ ግዛቸው በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለነበራችሁ የፀጥታ አካላት፣ የክልሉ ወጣቶች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ባለሀብቶቻችንና ለመላው የክልሉ ህዝቦች አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በበዓሉ የታየው ትህናትና ፣ ጨዋነት፣ መልካምነት ፣ ቁርጠኝነትና አንድነት በሌሎች የክልሉ የሰላም፣ የልማትና የአብሮነት ስራዎች ላይም እንዲደገም ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.