Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካው ኩባንያ የተመረተው የኮቪድ19 ክትባት የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞደርና የተሰኘው የአሜሪካው ኩባንያ ያመረተውን የኮቪድ19 ክትባት በሰዎች ላይ ለመሞከር ወደ ሚያስችለው ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።

የባዮ ቴክኖሎጂው ኩባንያ ያመረተው ክትባት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ ሙከራ እንደሚገባም አስታውቋል።

ኩባንያው በመጀመሪያ ሙከራው 45 ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን የምርምሩ ተሳታፊዎችም ቫይረሱን የመከላከል አቅም እንዳገኙ ተገልጿል።

በቀጣይ በሚያካሂደው የሙከራ ሂደት 30 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉም ነው የተባለው።

ምርምሩ እስከ ፈረንጆቹ ጥቅምት 2022 ድረስ ይቀጥላልም ተብሏል።

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.