Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን መድረሱ ይፋ ሆኗል።

በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ደግሞ 58 ሺህ መድረሱ ነው የተነገረው።

ሆኖም የአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥለውት የነበረው እገዳ እያነሱ ይገኛል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙት 3 ሚሊየን 177 ሺህ 756 የደረሰ ሲሆን 217 ሺህ 207 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

ቢሁታን ፣ ሞርሺየሰ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ እና የመን በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና የተያዙ ሰዎችን በዝቅተኛ ደረጃ የተመዘገበባቸው ሀገራት ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.