Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 20፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)በአሜሪካ በኮቪድ-19 ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ 276 መድረሱን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።

ከዚያም ባለፈ በሀገሪቱ 1 ነጥብ 69 ሚሊየን የሚሆኑት  ደግሞ በበሽታው መያዛቸው ተገልጿል።

ይህም  ቁጥር በዓለም ዙሪያ በወረርሽኙ ከተያዙት ከጠቅላላው 30 በመቶውን ይይዛልም ነው የተባለው ፡፡

ይህም አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱባት ዜጎች ቁጥር በቬትናም፣በኢራቅ፣በአፍጋኒስታንና በኮሪያ ጦርነቶች በድምሩ ከሞቱት ዜጎች በላይ መሆኑም ነው የተነገረው።

በሌላም በኩል አሜሪካ በሟቾችም ሆነ በወረርሽኙ በተያዙ ሰዎች ቁጥር አንደኛ ብትሆንም ከህዝቧ ብዛት አንጻር ሲሰላ በዓለም 9ኛዋ ሀገር መሆኗን ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ  ገልጿል

በአገሪቱ የመጀመሪያው  በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሪፖርት የተደረገው በፈረንጆቹ  ጥር 21 ቀን በዋሽንግተን ግዛት  መሆኑ ይታወሳል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው  የተያዙ ሲሆን 354 ሺህ 984 የሚሆኑት ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.