Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ከአውፓውያኑ መጋቢት ወር ማገባደጃ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና በአንድ ቀን የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በኒው ዮርክ በ24 ሰዓት 84 ሰዎች ሲሞቱ ከቀደመው ቀን ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛው መሆኑን የተናገሩት የግዛቷ አስተዳዳሪ አንድሪው ኮሞ በቀደመው ቀን የሟቾች ቁጥር 109 እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተጠቃችው የአሜሪካ ግዛቷ ኒውዮርክ ወረርሽኙ በተፋፋመበት ሚያዚያ ወር በየቀኑ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያልፍ ነበር፡፡

አስተዳዳሪው የኒውዮርክ ከተማን ጨምሮ በየትኛውም የግዛቷ አካባቢ ህጉን በተከተለ መንገድ እስከ አስር የሚደርሱ ሰዎች አንድ ላይ መሰባሰብ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በኒውዮርክ እስካሁን ከ28 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል፡፡

አሜሪካ በአለም ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ያለባት አገር ስትሆን እስካሁን ኮሮና ቫይረስ የ96 ሺህ ዜጎቿን ህይወት ቀጥፏል ።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.