Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4፣ 20121(ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊየን ማለፉ ተገለጸ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ እየተቀጣች ያለችው አሜሪካ 162 ሺህ 455 ዜጎቿ በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉም ተሰምቷል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃ በአሜሪካ በአንድ ቀን ከ54 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮሮና ቫይረስ ባለባቸው ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ሃገር ሆናለች፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በየእለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እንዲሁም ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ፡፡

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኙ ከ20 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተይዘዋል፡፡

ብራዚል፣ ህንድ፣ ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካ ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባቸው ሃገራት ናቸው፡፡

 

 

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.