Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የኮቪድ19 ቫይረስ ስርጭት በእጥፍ እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኮቪድ19 ቫይረስ ስርጭት በእጥፍ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡
የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ባደረገው መረጃ፥ በአሜሪካ ለወራት እየቀነሰ የነበረው የኮቪድ19 ቫይረስ ስርጭት መጠን ካለፉት ሶስት ሳምንታት ወዲህ እንደገና እያሻቀበ ነው፡፡
የዴልታ ዝርያ ያለው የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተሰራጨ መምጣት፣ የክትባት አቅርቦት መዘግየት እና በአሜሪካ የነጻነት ቀን ላይ ብዛት ያለው ህዝብ አደባባይ መውጣቱ ለቫይረሱ ዳግም መጨመር ምክንያት ሳይሆን አልቀረም ተብሏል፡፡
ሰኞ ዕለት ብቻ 23 ሺህ 600 ሰዎች በቫይረሲ ሲያዙ ፥ ይህም በፈረንጆቹ ሰኔ 23 ቀን ከተመዘገበው 11 ሺህ 300 ቁጥር አንጻር ከፍ ያለ ሆኖ ታይቷል፡፡
ማይን እና ደቡብ ዳኮታ ግዛቶች ቫይረሱ በስፋት የተስፋፋባቸው ቦታዎች ሆነዋል፡፡
የቫይረሱን መስፋፋት ተከትሎም የተከተቡም ሆኑያልተከተቡ ዜጎች ማስክ እንዲያደርጉ፣ ከሌሎች ሀገራት የሚገቡ መንገደኞችም ለ10 ቀናት በማቆያ እንዲቆዩ፣ እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች ህዝባዊ ስብሰባዎች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች እንዳይገኙ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ስለ ኮቪድ19 የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችን ዜጎች ከማጋራት ሆነ ከመፃፍ እንዲቆጠቡ መመሪያ ወጥቷል፡፡
የጆን ሆፕኪንስ አሁናዊ መረጃ እንደሚያመላክተው እስከ ረቡዕ ድረስ 33 ነጥብ 9 ሚሊየን ዜጎች በኮቪድ19 ሲያዙ፥ 607 ሺህ 763 ዜጎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.