Fana: At a Speed of Life!

በአራተኛው የኢትዮጵያ የንግድ ትርኢት የ10 የተለያዩ አገራት ኩባንያዎች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና፣ ምግብና መጠጥ ማቀነባበርና የፕላስቲክ ህትመት የንግድ ትርኢት የ10 የተለያዩ አገራት ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ አዘጋጅጆቹ ተናገሩ።
አራተኛው የኢትዮጵያ የግብርና፣ ምግብና መጠጥ ማቀነባበርና የፕላስቲክ ህትመት የንግድ ትርኢት ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
የንግድ ትርኢቱ አዘጋጅ የሆኑት ፌር ትሬድ እና የፕራና ኤቨንት አዘጋጆች ከተለያዩ ተሳታፊ አገራት ኤምባሲ ተወካዮች ጋር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የፕራና ኤቨንት ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ለማ፤ መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በከፍተኛ ወጪ መገንባቱን አንስተዋል።
የንግድ ትርኢትና ባዛር በኢንዱስትሪ ፓርክ የሚሰሩ ባለሃብቶች ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ እና ተሞክሮ ለመቅሰምና አላማቸውን ለማሳደግ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በንግድ ትርኢቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች እንዲሁም ከቱርክ፣ ጀርመን፣ ኢጣሊያ፣ ፈረንሳይ፣ ህንድን ጨምሮ የ10 አገራት 40 ኩባንያዎችና ድርጅቶች ይሳተፋሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የፌር ትሬድ መስራች ማርቲን ማሬዝ፤ የንግድ ትርኢቱ የእውቀትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጠቃሚ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም የሀገር ውስጥ አምራቾች የእውቀት ሽግግር ለመፍጠርና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክና ኢንዱስትሪ ልማት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ አያልነህ አባዋ ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.