Fana: At a Speed of Life!

በአራት አቅጣጫ የገባው የጠላት ሀይል አብዛኛው ተደምስሷል – የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽንፋ በኩል በአራት አቅጣጫ የገባው የጠላት ሀይል አብዛኛው መደምሰሱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለፋን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናገሩ፡፡

በሱዳን በተለያዩ የማሰልጠኛ ተቋማት የሰለጠኑ 1 ሺህ 200 የጁንታ አባላትና ቁጥራቸው ከ250 በላይ የሚሆኑ ፅንፈኛ የቅማንት ኮሚቴ ተላላኪዎች በጋራ በመሆን በሽንፋ ንዑስ ወረዳ በአራቱም አቅጣጫ ለመውረር የተደረገው ጥረት ከንቱ ሁኖ ቀርቷል ብለዋል አቶ ደሳለኝ ጣሰው።

ዋና አስተዳዳሪው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳረጋገጡት የወገን ጦር አስቀድሞ መረጃ ስለነበረው የጠላት ሀይል በገባበት ቦታ አይቀጡቅጣት እንዲቀጣ አድርጎታል ብለዋል።

ከነሀሴ 26 ጀምሮ በተደረገው ውጊያ 462 የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ ሲሆን፣ 39 የሽብር ቡድኑ አባላት የተማረኩ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል።

ውጊያ በተካሄደበት ሽንፋ ወንዝ አቅራቢያ የጠላት ሀይል አካባቢውን በውል የተገነዘበ ባለመሆኑ ሽንፋ ወንዙ ከ100 በላይ የጁንታውና መሰሎችን ሀይል ጠራርጎ መውሰዱን አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

በርካታ የጠላት የግልና የቡድን መሳሪያዎች ገቢ ተደርገዋል ያሉት አስተዳዳሪው፣ ከተወገዱ እና ከተመረኩ የጥፋት ሀይሎች ልዩ ልዩ መረጃዎች የተገኙ ሲሆን ተቆርጦ የቀረውን የጠላት ሀይል የማፅዳት ስራ ቀጥሏል ብለዋል።

ለተመዘገበው ድል የመከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ወጣቱ ያደረገው ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ ይህም በቀጣይ የወራሪው ሀይል እስኪደመሰስ ድረስ መቀጠል እንዳለበት ነው የገለፁት።

የዞኑ ህዝብ ያሳየው የደጀንነት ተግባር በገንዘብና በአይነት የተለየ መሆኑን ያወሱት አስተዳዳሪው ይህም ግንባር ድረስ በመዝመት የተገለጠ ነው ብለውታል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.