Fana: At a Speed of Life!

በአራት የገጠር ቀበሌዎች የተገነቡት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአራት የገጠር ቀበሌዎች የተገነቡት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ፡፡
እስካሁንም በሶማሌ ክልል ቆርሌ፣ በኦሮሚያ ክልል ሚኖ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አልባሳና በጋምቤላ ክልል አንጎጌ ቀበሌዎች የተገነቡት የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በቀሪዎቹ ስምንት የገጠር ከተሞችና መንደሮች የሚገነቡት ደግሞ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
የፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ ወጪም በአለም ባንክ የሚሸፈን ሲሆን በድምሩ 3 ነጥብ 8 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫሉ፡፡
ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከ71 ሺህ በላይ ደንበኞችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልፆ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግም ከፍተኛ አስተዋጾኦ ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡
እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የጤና ተቋማት፣ የእርሻ ማዕከላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የውሃ ተቋማትና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.