Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን አራት ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርሲ ዞን አራት ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የዞኑ እርሻ እና ተፈጥሮ ፅህፈት ቤት ገለፀ።
 
የበረሃ አንበጣ መንጋው በዞኑ ዶዶታ ወረዳ ቆሮ ደጋጋ ቀበሌ በ12 ሄክታር መሬት ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱንም ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።
 
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የኬሚካል ርጭት ተደርጎ መቆጣጠር ቢቻልም የአንበጣው መንጋው በሎዴ ሄጦሳ፣ ስሬ እና ጀጁ ወረዳዎች በመግባት ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጸው።
 
የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባቡ ዋቆ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ አሁን ላይ የአንበጣ መንጋው በጀጁ ወረዳ በ1 ሺህ ሄክታር ላይ ያረፈ በመሆኑ ትልቅ ጉዳት እንዳያደርስ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
 
በመሆኑም አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች የአንበጣ መንጋው በአካባቢያቸው ሲከሰት ፈጥነው ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክረ ሀሳብ መሰረት እንዲከላከሉም ጥሪ አቅርበዋል።
 
በማርታ ጌታቸው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.