Fana: At a Speed of Life!

በአስራዎቹ ዕድሜ ክልል ላይ የምትገኝን ልጃገረድ የሚመስለው የ42 ዓመቱ ጎልማሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአስራዎቹ ዕድሜ ክልል ላይ የምትገኝ ቆንጆ የትምህርት ቤት ልጃገረድ የሚመስለው የ42 ዓመቱ ጎልማሳ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።

ትኩማ ታኒ የተባለው የ42 ዓመት ጃፓናዊ የፊት ገጽታ ለብዙዎች እንግዳ ሆኗል።

የሙዚቃ ባለሙያው ትኩማ ታኒ በፈረንጆቹ 1977 ነበር የተወለደው።

ግለሰቡ ከልጅነቱ ጀምሮ በተለያዩ የኪነ ጥብብ ዘርፎች ላይ እየተሳተፈ አሳልፏል።

ዕድሜው 28 ሲደርስም በጃፓን ሮክ ሙዚቃ ቡድን ድምጻዊ ሆኗል፤ በሙዚቃ ቡድኑ ውስጥ የተሰጠውን ስራ በተገቢው ሁኔታ ሲያከናውን የቆየው ትኩማ፥ ዕድሜው 31 ዓመት ሲደርስ አንድ ለየት ያለ ሃሳብ ለመተግበር ያስባል።

ድምጻዊው በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ቆንጆ ልጃገረድን በትክክል መምሰል መቻል ደግሞ ሃሳቡ ነበር።

ይህን ለመተግበር ባደረገው ጥረትም ሃሳቡ ተሳክቶለት የውብ ልጃገረድ ገጽታን መላበስ ችሏል።

ይህን ገጽታውን ከተላበሰ በኋላ የልጃገረድ መልክ እና ቁመና እንዲሁም አለባበስን በማስመሰል ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።

ይህን እቅዱን ለማሳካት ግን የተለየዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና መዋቢያ ቁሶችን እንደሚጠቀም ተገልጿል።

47 ኪሎ ግራም ክብደት እና 1 ሜትር ከ62 ሴንቲ ሜትር ቁመት ያለው ትኩማ፥ ይህ ተክለ ሰውነቱ ልጃገረድ ለመምሰል የሚያደርገውን ጥረት እንዳቀለለት ይናገራል።

ምንጭ ፦ኦዲቲ ሴንትራል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.