Fana: At a Speed of Life!

በአሶሳ የማርብል ክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከል ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የማርብል ክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከል አስጀመረ።

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር አቶ ታከለ ኡማ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ጋር በመሆን በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ፍሬያማ እና ለወደፊት ስራዎች መሰረት የጣለ መሆኑን ሚኒስትሩ አቶ ታከለ ኡማ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።

“ሁሉም በመናበብ እና በትብብር ከሰራ ተፈጥሮ የቸረችውን እምቅ ሀብት ለሀገራችን እድገት ማዋል እንችላለ”ን ሲሉም ገልጸዋል።

ከምድር በታች ሃብት የታደለችውን የቤኒሻንጉል ክልልን ለማልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሉ መንግሥት ጋር የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከቤኒሻንጉል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከውይይቱ በኋላ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.