Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ተወርረው የነበሩ ቀሪ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ እየወጡ ነው

ሰበር ዜና

በአሸባሪው ህወሓት ተወርረው የነበሩ ቀሪ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ እየወጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአሸባሪው ሕወሐት ተወርረው የነበሩት ቀሪ ከተሞች፣ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በወሰዱት ማጥቃት ነጻ እየወጡ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ሠራዊቱም ወደ መርሳ እየገሠገሠ ነው።

በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከአሸባሪው የሕወሐት ወራሪ ነጻ ወጥተዋል።

በሁሉም ግንባሮች የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደውስጥ ዘልቀው በመግባት የተበታተነውን አሸባሪ ኃይል ቀለበት ውስጥ አስገብተው በመደምሰስ ፣ ወራሪው ኃይል የዘረፈውን ንብረት እንዲሁም የያዘውን መሣሪያና ትጥቅ ይዞ እንዳይወጣ እያደረጉት ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.