Fana: At a Speed of Life!

በአብዬ በሚገኙ ተቀናቃኝ ጎሳዎች መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብዬ ግዛት የሚገኙት የሚስሪያ እና ዲንካ ጎሳዎች መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ፡፡

በሚስሪያ በኩል ጃዕሚ አልሲድቅ እንዲሁም በዲንካ ጎሳ በኩል ደግሞ ዋር ሀመዲን ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

በአብዬ አሚት በምትባል ከተማ በተካሄደው የሁለቱ ጎሳዎች የጋራ ስብሰባ በአካባቢው በተለያየ ጊዜ ይከሰት የነበረውን ግጭት በማስወገድ በጋራ ሰላምን ለማስፈን ስምምነት ደርሰዋል፡፡

በስምምነቱ አካባቢውን ከተኩስና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የፀዳ ለማድረግ፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት፣ የድንበር አካባቢ ወንጀሎችን እና ለበርካታ ጊዜያት በግጦሽ ሳርና የመጠጥ ውሃ ምክንያት ይከሰት የነበረውን የእርስ በእርስ ግጭት ለማስቆም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ በተባበሩት መንግሥታት የአብዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ሃይል (ዩኒስፋ) የሰሜን ሴክተር ላይዘን ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ዋኘው አለሜ እንዲሁም የ23ኛ፣ 24ኛ እና 25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዦች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.