Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የልኡካን ቡድን ወደ አሜሪካ ተጓዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ወደ አሜሪካ ተጓዘ።

ቡድኑ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከግብጽ እና ከሱዳን አቻው ጋር ለመወያየት ነው ማምሻውን ወደ አሜሪካ የተጓዘው።

በልኡካን ቡድን ውስጥ የኢፌዲሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለን ጨምሮ ከፍተኛ የውሃ ምህንድስና እና የህግ ባለሙያዎች መካተታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የልኡካን ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 28 እና 29 ቀን 2020 የአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እና የዓለም ባንክ ከፍተኛ ሃላፊዎች በታዘቢነት በሚሳተፉበት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል አና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ ህጋዊ ማዕቀፍ ለማስቀመጥ የሚያስችል ውይይት እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.