Fana: At a Speed of Life!

በአንዋር መስጊድ እና አካባቢውን የማፅዳት መርሃግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገ ዕለት የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ በአንዋር መስጊድ እና አካባቢውን የማፅዳት መርሃግብር ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት በነገው ዕለት ለሚከበረው 1ሺህ 496ኛው የመውሊድ በዓልን የአንዋር መስጊድን እና አካባቢውን የማፅዳት ስራ ተካሂዷል።
በፅዳት ስራው ከተለያዩ የዕምነት ተቋማት የመጡ የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ አመራሮች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣የጽዳት ሰራተኞች እና ልዩ ለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ ክብረ በዓላቶችን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድምቀቶች በመሆናቸው የሚከበሩበትን ስፍራዎች በማፅዳትና በማስዋብ የአብሮነነትን ፣የአንድነት፣ የመቻቻልና የመተሳሰብ ባህላችንን እንዲጠናከር ያደርጋል ሲሉ በጽዳት ስራው የተሳተፉ የሀይማኖት አባቶች መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.