Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ሳምንት ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 16 ተሽከርካሪዎችና 17 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

27 ሚሊየን 309 ሺህ 350 ብር ግምታዊ ዋጋ የወጣላቸው የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች ሲሆኑ፥ 3 ሚሊየን 773 ሺህ 410 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው እቃዎች ደግሞ የወጪ ኮንትሮባንድ ናቸው ተብሏል፡፡

ወደ ሀገር ሲገቡ የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የብር ጌጣጌጥ፣ ሲጋራ፣ የነብር ቆዳ፣ ኮስሞቲክስ፣ መለዋወጫ፣ ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጥ፣ መድሃኒት፣ የተለያዩ መሳሪያዎችና ልዩ ልዩ ተተኳሽ ጥይቶች፣ የዝሆን ጥርስ እና ጫማ ናቸው፡፡

115 ሺህ 470 የኢትዮጵያ ብር፣ 65 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር፣ 22 ሺህ 800 የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ድርሃም፣2 ሺህ 700 የሳዑዲ ሪያል፣ 3 ሺህ 400 ዩሮ፣ 900 ፓውንድ፣ 13 በሬዎች፣ አደንዛዥ ዕጽ፣ 505 ኪሎ ግራም ቡና ከሃገር ሊወጡ ሲሉ የተያዙ ናቸው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የጉምሩክ ሰራተኞች፣ የፌደራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና ህብረተሰቡ በጋራ ባደረጉት ጥረት የተያዙ መሆናቸውንም ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.