Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ቀን ብቻ በኢትዮጵያ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 22 ሺህ 252 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የዛሬው ውጤት በሀገሪቱ በአንድ ቀን ብቻ የተመዘገበ ከፍተኛ ቁጥር ሆኗል።
ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ 894 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመልክተዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ17 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 509 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 199 ሰዎች በፅኑ መታመማቸውንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.