Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ዓመት ውስጥ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በዓለም 60 ሚሊዮን ዜጎች ተፈናቅለዋል

አዲስ አበባ፣ግንቦት 12፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በፈረንጆቹ 2021 በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በዓለም ላይ 60 ሚሊዮን ዜጎች መፈናቀላቸውን ሪፖርቶች አመለከቱ፡፡

በ2021 በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ከተፈናቀሉ ሰዎች ከ18 ዓመት በታች የሆናቸው ዜጎች መሆናቸውን የውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል (IDMC) እና የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት (NRC) ባወጡት ሪፖርት አስታውቀዋል።

ይህ አሃዝ ከዓመት ዓመት እየጨመረ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን ይህም በአስር ዓመታት ውስጥ የታየ ከፍተኛ የተፈናቃዮች ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል ነው የተባለው፡፡

የውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አሌክሳንድራ ቢላክ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ የዩክሬንን ጦርነትን በመጥቀስ በ2022 የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ያን አጌላንድ በበኩላቸው፥ ዓለማችን ችግር ውስጥ መሆኗንና እንደዚህ አይነት ችግር ዓለም ገጥሟት አያውቅም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የዓለም መሪዎች በግጭት አፈታት ዙሪያ የፖሊሲ ለውጥ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡት ዋና ፀሃፊው፥ ይህም እየተባባሰ የመጣውን የሰው ልጅ ችግር ያስቆመዋል የሚል እምነት እንዳላቸው መናገራቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.