Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ባለፉት 16 ቀናት በመኪና እና ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ባለፉት 16 ቀናት በመኪና እና ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ማህበረሰቡም ተጥሎ የሚያገኘውን የጦር መሳሪያ ጉዳት እንዳያደርስበት ከመነካካት በመቆጠብ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ ሃይል ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል።

የአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንደተናገሩት÷ ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ የእጅ ቦምብን ጨምሮ 26 ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 732 መሰል ጥይቶች ተይዟል።

በፍተሻው 129 የተለያዩ ሽጉጦችና 1 ሺህ 388 መሰል ጥይቶች እንዲሁም 27 የተለያዩ ጠመንጃዎች መያዛቸውንም ገልጸዋል።

በፍተሻው የጸጥታ አካላት የደንብ ልብሶች መገኘታቸውንም ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል።

የመገናኛና ወታደራዊ ሬዲዮዎችም ከተያዙት መሳሪያዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በእግረኛና በመኪናዎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም 41 የተለያዩ አይነት ሽጉጦች ከ254 መሰል ጥይቶቻቸው ጋግ ተይዘዋልም ነው ያሉት፡፡

በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የእጅ ቦምቦች፣ ጠመንጃ፣ ሽጉጥና ጥይቶች ተጥለው የተገኙ ሲሆን በተለይ ቦምቦች በሰዎች ላይ ሞትና ጉዳት ማድረሳቸውን አነስተዋል።

ፖሊስ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን የመያዝ ሂደቱን እንደሚያጠናክር በመጥቀስም፥ ህዝቡ መረጃና ጥቆማ የመስጠት ሚናውን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በተለያዩ ቦታዎች ወድቀው የሚገኙ የጦር መሳሪያዎች ጉዳት እንዳያደርሱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም መክረዋል።

ከቀናት በፊት በልደታ ክፍለ ከተማ ወድቆ ያገኙትን ቦምብ የነካኩ በጎዳና ላይ የሚኖሩ ልጆች ሞትና ጉዳት ማስከተሉን ለአብነት አንስተዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ወድቆ በሚያገኝበት ጊዜ ከመነካካት በመቆጠብ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ አካላት ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.