Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ከ6 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ19 ወረርሽኝን ተከትሎ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ እና በህገ ወጥ ተግባር በተሳተፉ ከ6 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ በ115ቱ ላይ በፍርድ ቤት ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ህገ ወጥ ተግባራትን አስቀድሞ የመከላከል፣ ገበያን የማረጋጋት እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪን ለማስቀረት የቁጥጥር ስራዎች ተሰርተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና በህገ ወጥ ተግባራት የተሳተፉ 6 ሺህ 165 የንግድ ድርጅቶች እና ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን አቶ አብዱልፈታ ተናግረዋል።

በዚህም በ115 የንግድ ድርጅቶች ላይ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶ ጉዳያቸው እየታየ ሲሆን የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ እና በግብይት መመሪያው መሰረት ንግድ በማይፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድም አውስተዋል።

ሸማቹ ማህበረሰብም የወጣውን አዋጅ ተግባራዊ በማድረግ የቫይረሱን ተጋላጭነት በመቀነስ እና አካላዊ እርቀትን ጠብቆ መገበያየት እንዳለበትም አመልክተዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ነው

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.