Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላይ ተላልፎ የነበረው እገዳ ተነሳ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላይ ተላልፎ የነበረው እግድ መነሳቱ ተገለፀ።
የአግልግሎት እገዳው ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን የከተማ አስተዳደሩ የፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር ከነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መሬትና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱ ይታወሳል።
የከተማ አስተዳደሩ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሲያከናውን የነበረውን የማጥራት ስራዎች ማጠናቀቅ ችሏል።
በመሆኑም ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት እና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል እንዲያስችል የተጣለው እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.