Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 15 ሺህ 834 ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 15 ሺህ 834 መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ እስከዛሬ ለ289 ሺህ 794 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 15 ሺህ 834 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ ባለፉት 24 ሰአታት ለ3 ሺህ 591 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 446 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ10 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 5 ከአስከሬን ምርመራ 5 ደግሞ ከጤና ተቋም መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.