Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 867 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 132 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በዛሬው እለት በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 157 ሰዎች ውስጥ 132 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ በአጠቃላይም በመዲናዋ 3 ሺህ 867 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።

በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 132 ሰዎች መካከል 33 ሰዎች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፥ 21 ሰዎች ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 17 ሰዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ ናቸው።

በአጠቃላይም እስከአሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 799 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ጉለሌ 438፣ ቦሌ 539 እንዲሁም ልደታ ክፍለ ከተማ 407 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.