Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት እንደሚገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ከነገ ጀምሮ 560 የግል ማህበራት አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
 
የከተማ አስተዳደሩ ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ ነው የተጠቆመው፡፡
 
በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ አድርገዋል።
 
በዚህ ወቅትም 121 ሚሊየን ብር ድጎማ የተደረገላቸው 560 አውቶብሶች ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ አስተዳደሩ መከራየቱን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታቀዋል።
 
ምክትል ከንቲባዋ 3 ሺህ አውቶብሶችን በግዢ ለማስገባት የከተማ አስተዳደሩ በሂደት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።

 

አውቶቢሶቹ ለአንድ ሳምንት ለህዝባችን በነፃ አገልግሎት በመስጠት እፎይታን እንደሚሰጡም ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል።

የነዋሪዎችን ችግር መፍታት የእኛም ሃላፊነት ነዉ ብለው የዚህ መፍትሄ አካል ለሆኑት የሃገር አቋራጭ አውቶቢስ ማህበራት  ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.