Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የመሬት ኦዲትና ምዝገባ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

ምዝገባው ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ያለመ መሆኑንም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ክንቲባ ኢንጂር ታከለ ኡማ የምዝገባ እና ኦዲት ሂደቱን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከነገ ጀምሮ መካሄድ የሚጀምረው የምዝገባ እና ኦዲት ሥራ ከመሃል ከተማ እስከ ዳር የአርሶአደሮች ይዞታን ጭምር ያካተተ መሆኑም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በተለይም ለህገወጥ ወረራ ተጋላጭ የሆነው የአርሶ አደሮች ይዞታን በመመዝገብ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲኖራቸው እንደሚደረግም ነው ያስታወቁት።

ምዝገባው በቴክኖሎጂ አሰራር የተደገፈ እንዲሆን ከሳይንስ እና ኢኖቬሺን ሚንስቴር ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

በማስፋፊያ አምስት ክፍለ ከተሞች ላይ የሚገኘው የአርሶአደሮች መሬት ምዝገባ እስከ መስከረም 30 እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ምዝገባው በተለይም አርሶአደሮች በደላላ ተታለው ያለአግባብ መሬታቸው እንዳይወሰድ እና በህገወጥ መንገድ እንዳይወረር ለመከላከል እንደሚረዳ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.