Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢድ አልፈጥር  የሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በአዲስ አበባ የተካሄደው 1ሺ442ኛው የኢድ አልፈጥር  የሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ጎዳናዎች እንዲሁም በከተማዋ  ልዩ ልዩ ስፍራዎች የተካሄደው  የኢድ አልፈጥር  ረመዳን የኢድ ሶላት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢድ አልፈጥር ሶላት በሰላም እንዲጠናቅ ኮሚሽኑ እቅድ በማውጣት በርካታ የሰው ኃይሉን በወንጀል መከላከል ስራ ላይ አሰማርቶ ከሚመለከታቸው ሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በጋራ በመስራቱ የኢድ ሶላቱ  በሰላም መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ለበዓሉ በሰላም መከበር የከተማው ነዋሪ በተለይም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጉን እና ህብረተሰቡ የፀጥታው ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አመለካካት በመያዝ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ኮሚሽኑ አስታውሷል።

ነዋሪው እያበረከተ ላለው ቀና ትብብር እንዲሁም ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑ አያይዞም የከተማውን ጸጥታ ለማስከበር በሚሰሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡንአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.