Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና የጸጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና የጸጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከክልሉ ህዝብና መንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጡ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌደራል ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር በሕግ ማስከበር ሂደቱ የነበሩ እውነታዎችን ለባለሀብቶች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አቶ አገኘሁ ተሻገር አሁን የክልሉ መሪዎች ወቅቱ የሚጠይቀውን በጋራ ቆሞ የመጣን ችግር ሁሉ በጋራ መታገል ላይ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ሕግ የማስከበር ስራ ክልሉ ያለውን ሁሉ አድርጓል፤ በቀጣይ የጀመረውን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል ባለሀብቶች እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በህዝብ ላይ ሲደርስ የቆየው የፍረጃና የሴራ እሳቤ እውነታው መጋለጡን ጠቅሰዋል፡፡
ጁንታው መሸነፉን ገልጸው ቀጣዩ ምዕራፍ በጋራ ቆመን የኛን የቤት ሥራ የምንሰራበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ሕግ በማስከበር ሂደቱ የተለያዩ ወጪዎችን ማውጣቱን ዶክተር ፋንታ ጠቅሰዋል፡፡
ባለሀብቶች የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብም አለኝታነታቸውን በተግባር አሳይተዋል ብለዋል፡፡
በዕለቱም ከ3 መቶ 76 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ቃል መገባቱን አብመድ ዘግቧል።
የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በግንባር በመሰለፍ ለፈጸመው ተጋድሎ በመድረኩ ተሳታፊዎች በህሊና ጸሎት እና እውቅና በመስጠት ታሰቧል።
መድረኩም ባለሀብቱ እና መንግስት ለክልሉ ሁለንተናዊ ለውጥት በጋራ ለመስራት ቃል የገቡበት ሆኖ ተጠናቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.