Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 2 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ሁለት ዘመናዊ ሆስፒታሎች ሊገነቡ መሆኑ ተገለጸ።

በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትና ያሉት ሆስፒታሎች የማስተናገድ አቅማቸው ባለመመጣጠኑ የሆስፒታሎችን ቁጥር መጨመር አስፈልጓል።

በከተማዋ ስድስት የመንግስት ሆስፒታሎች የሚገኙ ሲሆን፥ የማስተናገድ አቅማቸውም 1 ሺህ 557 ታካሚዎችን ብቻ ነው።

ይህንን ቁጥር ከፍ ለማድረግ እና አገልግሎቱን ለማስፋትም በንፋስ ስልክ ላፋቶ እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ሁለት ሆስፒታሎች ይገነባሉ ነው የተባለው።

ሁለቱ ሆስፒታሎች ሲጠናቀቁም 940 ታካሚዎችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖራቸው ተነግሯል።

በሆስፒታሎቹ ዲዛይን ላይም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየተወያዩበት ነው ሲል የዘገበው አዲስ ቴሌቪዥን ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.