Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 4ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በመጪው እሁድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ 4ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በመጪው እሁድ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

መርሃ ግብሩ የትራንስፖርት ቢሮ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው ተብሏል፡፡

በየወሩ በ4ኛው ሳምንት የሚከበረው የብስክሌትና እግረኞች ቀን በመዲዋ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስተዋወቅ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ማህበረሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ከማስቻሉ ባለፈ ብስክሌት አማራጭት የትራንስፖርት ስልት እንዲሆን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እገዛ እንደሚያደርግ መገለጹን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.