Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ298 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ298 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 156 ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው መርቀዋል።

ፕሮጀክቶቹ የትምህርት እና የጤና ተቋማት፣ የመስሪያ ቦታ ሼዶች፣ የስፖርት ማዘወተሪያ፣ የአደባባይ ማስዋብ ስራዎች፣ የጎርፍ መከላከያ ግንቦች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገልጿል።

ፕሮጀክቶቹ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና ግንባታቸው በጥራት እና በፍጥነት የተከናወነ መሆኑን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.