Fana: At a Speed of Life!

በአዳሚ ቱሉ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው በድሎ ሬጴ ቀበሌ ውስጥ ትናንት ማምሻውን መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽንናና ሚዲያ ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ ተናግረዋል፡፡

በዚህም አሽከርካሪውን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ወደያውኑ ማለፉን አስታውቀዋል፡፡
አደጋው የደረሰው ከቡታ ጅራ ወደ ባቱ እየተጓዘ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ 16 ሰዎች ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ በመገልበጡ መሆኑን ኮማንደር አስቻለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ በአዳማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከአደጋው አራት ህፃናት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፉቸውን ኮማንደር አስቻለው አመልክተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.