Fana: At a Speed of Life!

በአድዋ መንፈስ ኢትዮጵያ ሀገራችንን ወደ ከፍታ ማማ እናሸጋግራለን – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአድዋ መንፈስ ኢትዮጵያ ሀገራችንን ወደ ከፍታ ማማ እናሸጋግራለን አሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡፡
የጋራ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል ብሄራዊ የምክክር መድረክ በሸገር ፓርክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሀገራችንን ወደተሻለ ከፍታ ለማድረስ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር ያሉብንን ችግሮች ለመፍታት የጋራ መፍትሄ ያሻልም ነው ያሉት፡፡
በአድዋ የአሸናፊነትና የፅናት መንፈስ የማንወጣው ችግር አይኖርም ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡
የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ከሚል እስካሁን ለስድስት ወራት የተደረገው ውይይት ፍሪያማ ነበር፤ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ያሉ ችግሮች ተነስተዋል ፤ለተሻለ ተግባቦት የተሻለ ውጤት ተገኝቶበታልም ብለዋል።
መድረኩን ያዘጋጁት ዴስቲኒ ኢትዮጵያ እና የሰላም ሚኒስቴር ናቸው፡፡
”ስልጡን ምክክር አዲስ የተስፋ ምዕራፍ” በሚል እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ ከ1 ሺህ 200 በላይ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት በሚካሄደው የምክክር መድረክ እንደ ሀገር ያሉ የጋራ ችግሮችን በመለየት የጋራ መፍትሄ ማፈላለግ ላይ ትኩረት ይደረጋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.