Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
እንደ ድርጅቱ ገለፃ በአህጉሩ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሳምንት ውስጥ ወደ 43 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡
ናሚቢያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቱኒዚያ ፣ ኡጋንዳ እና ዛምቢያ ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ብዙ ሰዎች ለህልፈት የተዳረጉበት ሃገራት ናቸው ተብሏል፡፡
ብዙ ሀገራት ኦክስጅንን ፣ የፅኑ ህሙማን መንከባከቢያ ክፍሎችንና ልዩ ባለሙያተኛ እጥረት አለባቸው ነው የተባለው፡፡
ይህም ግልፅ ማስጠንቀቂያ ነው ብለዋል የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞቲ፡፡
“ዴክሳሜታሲን” የተባለው መድሃኒት በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) እና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱ ታማሚዎች እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል፡፡
መድሃኒቱ በተለይም በመተንፈሻ መሳሪያዎችና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱትን ታማሚዎች የመሞት እድል የሚቀንስ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በአፍሪካ ከ150 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.