Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ1፣2012 ( ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው  ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አለፈ፡፡

22 ሺህ 114 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡

በአህጉሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በደቡብ አፍሪካ 538 ሺህ 184 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው 9 ሺህ 604 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በሌላ በኩል በታንዛኒያ ስለ ቫይረሱ የሚሰጠው መረጃ አናሳ መሆኑ ፈተና ነው ሲል የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል፡፡

በሃገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሳምንታዊ አሃዝ እየታተመ አለመሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ከዚህ ባለፈም  የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ቫይረሱ በሃምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ቫይረሱ ወደ መጥፋቱ እየተቃረበ ነው ሲል መግለፁ ይታወሳል፡፡

በዚህ እና በአህጉሪቱ በቂ ምርመራ ባለመደረጉ ቫይረሱ በትክክል ያለባቸውን ሰዎች ቁጥር ማወቅ አልተቻለም እየተባለም ይገኛል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የበሽታ መከላከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል  ወደ ታንዛኒያ ለመድረስ ጥረቱን ቢቀጥልም ከሃገሪቱ መንግስት ትክክለኛ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.