Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ 7 ሜዳሊያዎችን አገኘች

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ፍጻሜውን ባገኘው የአፍሪካ ልዩ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ 7 ሜዳሊያዎች በማግኘት አጠናቃለች።

የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር በግብጽ ካይሮ፥ በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በቦሽያ ስፖርት ተካሄዷል።

ኢትዮጵያም በአትሌቲክስ ስፖርት በአራት አትሌቶች ተወክላ ተሳትፎ አድርጋለች።

በውድድሩ በ100 ሜትር ከተገኘው 3 ሜዳሊያ በተጨማሪ በ200 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ላይ አንድ ወርቅና 3 ነሀስ ሜዳልያ አምጥታለች።

በ200 ሜትር ውድድር አትሌት ሚሊዮን ያደታ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

አትሌት ትግስት ኡጋሳ፣ አትሌት መአዛ ኤልያስ እና አትሌት ብሩክ አለማየሁ ደግሞ 3 የነሀስ ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።

በዚህም ውድድሩን 2 ወርቅ፣ 1 ብር እና 4 የነሃስ ሜዳልያዎች በድምሩ 7 ሜዳልያዎችን በማግኘት አጠናቃለች።

በውድድሩ የተካፈለው የኢትዮጵያ ልዩ ኦሊምፒክ ልዑክም ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባቱን የኢትዮጵያ የልዩ ኦሊምፒክ ዳይሬክተር ዮናስ ገብረማርያም ለጣቢያችን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.