Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያገረሽ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡

ድርጅቱ በአህጉሪቱ የሚታዩትን አዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች፣ የክትባት አቅርቦቶች መዘግየት እና ከክትባት መስጠት ጋር ተያይዞ ባሉ ክፍተቶች ምክንያት ቫይረሱ በድጋሚ ሊያገረሽ እንደሚችል ገልጿል፡፡

“በሕንድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውና ቢ.1.617 የሚል መጠሪያ የተሰጠው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በአንድ የአፍሪካ ሃገር መገኘቱ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ቢ1.351 የቫይረስ ዝርያ በ23 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ እየተዛመተ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በብሪታንያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ቢ1.1.7 ተብሎ የሚጠራው የቫይረስ ዝርያ ደግሞ በ20 ሃገራት እንደሚገኝም ነው የተገለጸው ፡፡

አንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት ክትባቶችን በማከፋፈል ረገድ አርአያ ሆነው መቆየታቸውን ያነሳው ድርጅቱ፥ በአፍሪካ ከ37 ሚሊየን ክትባቶች ውስጥ እስካሁን የተወሰዱት ግማሾቹ ብቻ መሆኑም አስታውቋል፡፡

በሕንድ የተከሰተው አሳዛኝ ሁኔታ አፍሪካ ውስጥ መከሰት የለበትም ያሉት የድርጅቱ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ሞኤቲ፥ ሁሉም ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም መንግስታት ጠንካራ የክትትልና የምርመራ ስርዓቶችን በመተግበር፣ የህክምና አቅማቸውን እንደገና በመገምገም እና በማጎልበት፣ የመተንፈሻ ኦክስጅንን ጨምሮ መድኃኒቶችን በማቅረብ እና ለጽኑ ህመምተኞች በቂ ማረፊያ ማዘጋጀት እንደሚገባቸው ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

እስካሁን በአፍሪካ ከ4 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው ከ123 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.