Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን 200 ሺህ በላይ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል በአህጉሪቱ የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን 202 ሺህ 918 መድረሱን ይፋ አደረገ፡፡

ማዕከሉ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት 28 ሺህ 276 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል፡፡

እንዲሁም 931 ሺህ 57 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን ጠቅሷል፡፡

ወረርሽኙ ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የጠነከረ ሲሆን 654 ሺህ 558 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

እንዲሁም በሰሜናዊ አፍሪካ 216 ሺህ 99፣ በምዕራብ አፍሪካ 156 ሺህ 604፣ በምስራቅ አፍሪካ 122 ሺህ 782 እና በማዕከላዊ አፍሪካ 52 ሺህ 878 በቫይረሱ መያዛቸውን ማዕከሉ በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡

ከሃገራት መካከል በደቡብ አፍሪካ 613 ሺህ 17 በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 13 ሺህ 308 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 520 ሺህ 381 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.