Fana: At a Speed of Life!

በአፍጋን መንግስት እና ታሊባን መካከል ውይይት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍጋን መንግስት እና ታሊባን መካከል የሚደረግ ውይይት ዛሬ ጀምሯል፡፡

በአፍጋኒስታን ለሁለት አስርት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት የዳረገው የአፍጋን መንግስትና ታሊባን ጦርነትን ለማስቆም ለድርድር ከሁለቱም በኩል የተውጣጣ ቡድን በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውይይቱን ጀምሯል፡፡

የአፍጋን መንግስት የቀድሞ የስለላ ሃላፊ የነበሩት ማሶም ሰታንክዛይ 21 አባላትን የያዘ የድርድር ቡድን ሲመሩ፤ በታሊባን በኩል ታጣቂ ቡድኑን በመምራት ማውላቪ ሃኪም እና የቡድኑ መሪ ሃይባቱላህ አክሁንዛዳ በውይይቱ ያሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ሁለቱም ወገኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የሚቀመጡበት ድርድር ሰኞ እንደሚጀመርም ነው የተነገረው ፡፡

በአፍጋን መንግስት ተደራዳሪ ቡድን በኩል አምስት ሴት ተወካዮች በውይይቱ ወቅት የሴቶች መብቶችን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ሃላፊነትን በመውሰድ ድርድሩ ላይ ይገኛሉም ነው የተባለው ፡፡

ወደ ስድስት ወር የፈጀው የአፍጋን መንግስትንና ታሊባንን ወደ ድርድር ለማምጣት የፈጀው ጊዜ ፈታኝ እንደነበረ ይነገራል፡፡

በሁለቱ ወገኞች የሚደረገው ድርድር ከወዲሁ ተስፋ እንደተጣለበት ቢጠቀስም ስምምነት ላይ ለመድረስ ከባድ ፈተናዎች ይጠብቁታል ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.