Fana: At a Speed of Life!

በኢሉ አባቦራ ዞን የዳሪሙ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን ተቃወሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦራ ዞን የዳሪሙ ወረዳ ነዋሪዎች የኦነግ ሸኔን ድርጊት ተቃወሙ፡፡

ነዋሪዎቹ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ኦነግ ሸኔ የወረዳዋን ነዋሪዎች ሰላም ሲነሳና ሲያሸብር መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

በወረዳዋ ቆላማ አካባዎች የልማት ስራዎች እንዳይከናወኑ እንቅፋት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ የቡድኑን የሽብር ተግባር በመኮነነን የአካባያቸውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ መነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡

የቡድኑ አባላት የነበሩና ህዝቡን የተቀላቀሉ ወጣቶች የኦነግ ሸኔን ድርጊት በማውገዝ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ከህዝቡ ጋር በመሆን የቡድኑን ጭካኔ እና የሽብር ተግባር በማጋለጥ እንታገላለንም ነው ያሉት፡፡

የኢሉ አባቦራ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ነጋሽ ህዝቡ ከመንግስት ጋር በመሆን ሰላሙን እንዲያስጠብቅ ጥሪ አስተላፈዋል፡፡

የወረዳዋ አስተዳዳር አቶ ደረጄ አያና በበኩላቸው ቡድኑ የልማት ስራዎችን ማደናቀፍ ብቻ ሳይሆን የመንግስት መዋቅር ህዝቡን በአግባቡ እንዳያገለግል እንቅፋት ሆኗል ብለዋል፡፡

በቡድኑ የሽብር ተግባር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ንብረት ወድሟልም ነው ያሉት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.