Fana: At a Speed of Life!

በኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ  ኤምባሲ በተቃዋሚዎች ጥቃት ደረሰበት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012(ኤፍቢሲ) አሜሪካ በኢራን የሚደገፈው የኢራቅ ታጣቂ ሀይል የአየር ጥቃት በመፈፀሟ የተቆጡ ኢራቃውያን በባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ የኤምባሲውን  የውጨኛ ክፍል ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ ወታዳሮች ወደ ተቃዋሚዎቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተነግሯል፡፡

ይህ የአሜሪካ ኤምባሲ የሚገኝበት የባግዳድ አካባቢ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት የሀገሪቱ መንግስት መስሪያ ቤቶች ማዕከል ነው፡፡

አሜሪካ ባሳለፍነው እሁድ ዕለት በኢራን በሚደገፈው የካታይብ ሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 25 የቡድኑ አባላት ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ይህን ታጣቂ ቡድን አሜሪካ  በኢራቅ የወታደራዊ ጣቢያ ላይ የሮኬትጥቃት በመፈፀም  አንድ ዜጋየን ገሏል ስትል ትወቅሳለች፡፡

ይህንን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር  የአሜሪካ ወታደሮች በታጣቂዎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት የኢራቅን ሉዓላዊነት የሚጥስ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የካታይብ ሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ኮማንደር አቡ ማህዲ አል  ሙሃንዲስ ቡድናቸው በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ላይ ከበድ ያለ የአፀፋ እርምጃ ሊወስድ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.