Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንትአማራጮች እንዳሉ የውጭ ኩባንያ ተወካዮች መሰከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት የሚያስችሉ አማራጮች እንዳሉ ማጤናቸውን የውጭ ኩባንያ ተወካዮች ተናገሩ።

ከ40 በላይ የተለያዩ የውጭና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የተሳተፉበት አራተኛው የኢትዮጵያ የግብርና፣ ምግብና መጠጥ ማቀነባበርና የፕላስቲክ ህትመት የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ተከፍቷል።

በንግድ ትርኢቱ ላይ የሩሲያ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ህንድ እና ቱርክ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ናቸው። በዚህም በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት የሚያስችሉ ሰፊ አማራጮች እንዳሉ ማጤናቸውን የውጭ ኩባንያ ተወካዮቹ ተናግረዋል።

በተጨማሪ አውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው ባለሃብቶች፣ ለአገር ውስጥ አምራቾች፣ ላኪዎች፣ አስመጪ ድርጅቶችና ኩባንዎች የንግድ ትርኢቱ ጥሩ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
የኢዜአ ያነጋገራቸው ዓለም አቀፍ አምራችና ላኪ ድርጅት ባለቤትና ተወካዮች የንግድ ትርኢቱ በኢትዮጵያ ያለውን የገበያ ሁኔታ በማየት ኢንቨስት ለማድረግ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።

የሞሃን ፒ.ኤል.ሲ ባለቤት ሞየሪ ኳተሪ፤ በኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ እድሎች መኖራቸውን በመጠቆም በፋብሪካ ምርት ሂደት ላይ ለመሰማራት የሚያስችሉ ሰፊ አማራጮች እንዳሉ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ በዘይት ምርት ላይ ያለውን የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን ለመሙላት የሚያስችል የኢንቨስትምንት ፍላጎት አለን ያሉት ደግሞ የጎ.ኤም ግሩፕ ኢንዲያን ኩባንያ የሽያጭና የማርኬቲንግ ኃላፊው አንኩር ቼትሮዳ ናቸው።

የሞሃን ፒ.ኤል.ሲ ባለቤት ሞየሪ ኳተሪ በበኩላቸው፤ የውጭ አገር ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ አገሪቷ ያላትን የሰው ሃይልና ጥሬ እቃ በመጠቀም እሴት ጨምረው ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

በሩሲያ የማዕድን ውሃና ለስላሳ መጠጦች አምራች የኤል.ሲ.ኤም ኩባንያ ኃላፊዋ በማዕድን ውሃና በለስላሳ መጠጥ ዘርፎች ላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሞየሪ ኳተሪ ጨምረው እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ የገበያ ችግር ባለመኖሩ እድሎችን በመጠቀም አትራፊ መሆን እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

የጀርመኑ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ላኪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ሰባስቲያን ሙለር፤ ኩባንያቸው በእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች በኢትዮጵያ ያለውን ገበያ ለመጠቀም የቢዝነስ አጋሮችን እያፈላለጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የንግድ ትርኢቱ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.