Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 26 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 26 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፥ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል።

ግለሰቡ የበሽታው ምልክት በማሳየቱ በላቦራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በአሁኑ ሰዓት ግለሰቡ በድሬዳዋ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ ሁለት (22) ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከያ መንገዶችን እና ከመንግስት የሚተላለፉ እርምጃዎችን ትኩረት በመስጠት እንዲተገበር የጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.