Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 16 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ16 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው በፌስቡክ ገጸቸው ባወጡት መረጃ፥ በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማቆያ ያሉ አጠቃላይ ሰዎች13 መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከታማሚዎች ውስጥ አንዱ ሙሉ በሙሉ ከቫይረሱ ማገገሙን የገለጹት ሚኒስትሯ፥በጽኑ የታመመ ሰው አለመኖሩን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለት ጃፓናውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.