Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 212 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 607 የላብራቶሪ ምርመራ 212 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ሺህ 181 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 155 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 18 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 12 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 10  ሰዎች አፋር ክልል፣ 8 ሰዎች ከድሬ ዳዋ አስተዳደር፣ 7 ሰዎች አማራ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው።

ከዚህ ባለፈ የ7 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 4 በአስከሬን ላይ ተደረገ ምርመራ፤ 3 ሰዎች ደግሞ በህክምና ማእከል ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው።

ይህንን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 146 መድረሱንም ነው ሚኒስቴሩ በእለታዊ ሪፖርት መግለጫው ያመላከተው።

በሌላ መልኩ በትላንትናው 105 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 717 ደርሷል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ297 ሺህ 542 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ሺህ 181 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 116 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 34 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 4 ሺህ 717 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ146 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.