Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 602 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺህ 221 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 602 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 67 ሺህ 515 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ12 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 72 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 553 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 27 ሺህ 638 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

38 ሺህ 803 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 289 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 184 ሺህ 473 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.