Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 689 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 10 ሺህ 605 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 689 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 66 ሺህ 913 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ15 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 60 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 420 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ስሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 27 ሺህ 085 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

38 ሺህ 766 ሰዎች በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 300 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 176 ሺህ 252 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.